Home Test 3

Test 3

22nd June, 2024

በየዕለቱ ረዘም ያለ የእንቅልፍ ጊዜ እንደሌለው የሚናገረው ጋዜጠኛ ዓለም ሰገድ ለዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በትክክል ባያውቀውም እንቅልፍ ያጣባቸው ቀናትም እንዳሉ ይናራል።እሱ በስልክ እና ላፕቶፕ ስክሪኖች ላይ ጊዜ የሚያሳልፍባቸውና አልፎ አልፎ ምሽት ላይ ቡና የሚጠጣባቸው ቀናት እንዳሉ ግን አልሸሸገም።ሆኖም “እንቅልፍ አጥቼ አድሬ ወደ ሥራ ስሄድ፣ ባህሪዬ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ከሰዎች ጋር መነጋገርን ያስጠላኛል፣ ትኩረት ማድረግ ያቅተኛል፣ እነጫነጫለሁ። እንቅልፍ ማጣት ያስፈራል” ይላል።በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ታናሽ ከሞተ በኋላ “በፍርሃት ተውጬ መተኛት አልቻልኩም” የምትለው ደግሞ ሮዳስ በየነ ነች።ጂቡቲ ውስጥ ሆና የወንድሟ መርዶ የተነገራት ጦርነቱ ካበቃ ከአንድ ዓመት በኋላ ነበር።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት እንደምትቸገር እና የተቆራረጠ የእንቅልፍ ሰዓታት እንደምታሳልፍ ትናግራለች።“ከሦስት ሰዓት በላይ አልተኛም። ሌሊት ድንገት ከነቃሁ ተመልሼ መተኛት አልችልም፤ ምንም ማድረግ ስለማልችል ከደከመኝ ብዬ ፊልም አያለሁ” ትላለች።እነዚህ ግለሰቦች ለቀናት እንቅልፍ ማጣታቸው ሥራቸው ላይ ተጽእኖ ያሳድርባቸዋል፤ በማኅበራዊ ሕይወታቸውም እርካታ እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል።አዎ፤ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሚፈጥረው ስሜት እና ጭንቀት እንዴት እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን።በተለያዩ ጊዜያት የታተሙ በርካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከአስር ጎልማሶች መካከል ቢያንስ አንዱ እንቅልፍ አልባ ሌሊት ያሳልፋል።ሌሊት ብዙ ጊዜ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁ ከሆነ እና ከነቃችሁ በኋላ ደግሞ ድካም የሚሰማችሁ ከሆነ ምናልባት ኢንሶምኒያ [እንቅልፍ ማጣት] ሊኖርባችሁ ይችላል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with