12/9/16 ዓ/ም
በንፋስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ!!
በ12/9/16 ዓ/ም ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሀላፊዎች በኮሌጁ በመገኘት የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ፡፡
የልምድ ልውውጡ እና ጉብኝቱ አላማ፡-
የኮሌጁ ኢንኩቤሽን ሴንተር እንዴት እንደተቋቋመ እና አሁን ስራወን እንዴት እያከናወነ አንደሆነ በማየት ልምድ ወስዶ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሆን፡ የኮሌጁ ዲን ወ/ሮ አዱኛ ካሴ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለው የኮሌጂን ታሪካዊ ዳራ እና በጠቃላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በፓወር ፖይን ገለጻ አቅርበዋል፡፤
ገለጻው እንደተጠናቀቀ የኢንኮቤሽን ሴንተር እና የሾች ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላ ከእንግዶቹ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷ፡፡
በመጨረሻም እንግዶቹ በአገኙት ልምድ እንደተደሰቱ እና ወደ ኮሌጃቸው ወስደው እንደሚተገብሩ በመግለጽ ለተደረገላቸው አቀባበል እና የጉብኝት ፕሮግራም ለኮሌጁ ምስጋና አቅርበዋል፡፤