Home GDC የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ጎበኙ

GDC የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ጎበኙ

27th May, 2024

German Develeopment Cooperation የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት
መጋቢት 19/2016 ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ German Develeopment Cooperation ጋር በመተባበር የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ለመጎብኘትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ውይይት ለማድረግ ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝቱም ካለፉት 5 ዓመትት ጀምሮ ከኮሌጁ ጋር የተሰሩ ስራዎችን (ከGIZ-QEP ጋር የInclusive Vocational Training for refugees and Host Community, Inclusive employment promotion Program, Entrepreneurship and Incubation Center (EIC) , ከSTEP III እና GOPA እና የትብብር ስልጠናን እንዲሁም ከKFW ጋር ለ Automotive, Electrical Electronics እና ለEIC የሚከናወኑ የግብአት ማሟላት ስራዎችን ገምግመዋል። በቀጣይም ኮሌጁን ከዚህ የተሻለ መስራት የሚችልባቸውን አማራጮች ያመላከቱ ሲሆን በጉብኝቱም በጣም ደስተኛ ማሆናቸውን የጠቀሱት የGerman Deputy Ambassador ናቸው።
በውይይቱም ከተለያዩ ካምፓኒ የተወጣጡ የካምፓኒ ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈው ልምዳቸውን አጋርተዋል። በቀጣይም ከኮሌጁ ጋር በሁለንተናዊ ትብብር አብረው እንደምሰሩ አረጋግጠው ስለተሰጣቸው ዕድልም ኮሌጁን አመስግነዋል።
ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ተወካዮች፣ የኮሌጃችን ዲኖችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪም እንግዶችን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
@nefassilk
.

Copyright © All rights reserved.

Created with